ስለ እኛ

እንተዋወቅ

ሎሬት የኪነ-ጥበብ ማሰልጠኛ ተቋም እና ሚሊዮን ፊልም ፕሮዳክሽን ዕውቅና ካገኘበት ከ2010 ዓ.ም ጊዜ አንስቶ በኪነ-ጥበቡ ዘርፍ በስፋት እያስተማረ እና እየሰራ ይገኛል።

ኪነ-ጥበብ

ኪነ-ጥበብ የአንድን ሀገር ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እሴቶቻችንን ትውፊት ባህሎቻችንን ለዛውን በጠበቀ ፣ አስተማሪና አዝናኝ በሆነ መልኩ ለማህበረሰቡ ለማቅረብ አንዱና ተመራጭ መንገድ ነው።

ሎሬት የኪነ-ጥበብ ማሰልጠኛ ተቋም እና ሚሊዮን ፊልም ፕሮዳክሽን በኪነ-ጥበቡ ዘርፍ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ ለአብነት ለመጥቀስ ያክል፡-

የኮሜዲ ውድድር

በኢትዮጵያ የመጀመርያ የሆነውን የኮሜዲ ውድድር በኤል ቲቪ እና በዋልታ ቲቪ ላይ ፕሮግራም በማዘጋጀትና በማስተላለፍ አዳዲስ ኮሜዲያንን ለማፍራት በቅተናል፡፡

በትወና ውድድር

ፀዳል በሚል ርዕስ በፋና ቲቪ ላይ ብዙ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን አፍርተናል፡፡

በሞዴሊንግ

በሞዴሊንግ፡- አሐዱ እንቁን ፍለጋ በሚል ዕር በአሃዱ ቲቪ ላይ ብዙ ሞዴሎችን አፍርተናል፡፡

የስራ እድል

ተቋማችን ለረጅም አመታት፡- ከ18,500 ሰው በላይ ለተለያዩ ድርጅቶች ተዋናይና ሞዴል በማቅረብ እንዲሁም በማሰራት ለብዙዎች የስራ እድል በስፋት በመፍጠር እንተወቃለን ፣ እየሰራንም እንገኛለን።

ሌሎች ስልጠናዎች

በተቋማችን ውስጥም በሞዴሊንግ ፣ በትወና ፣ በሁሉም ሙዚቃ መሳሪያ ስልጠና በመስጠት ፣ እንዲሁም በቪድዮ ኤዲቲንግ እያስተማርን ከ7,500 ሰው በላይ አስመርቀናል። በተለይ ለሴቶች እና ለህጻናት ፣ እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች 50% የክፍያ ቅናሽ አድርገን ስልጠና መስጠታችን ፣ በተጨማሪም፡- ለመንግስት ሰራተኞች በጉሩፕ ለሚመጡ ሰልጣኞች ሚኒቴሪዎችን ጨምሮ 50% ቅናሽ ማድረጋችን ልዩ ያደርገናል።

አጋሮቻችን