በመዝናኛው ኢንዱስትሪ ላይ ትልልቅ ሥራዎችን በመስራት የኢትዮጵያ የዲጂታላይዜሽን እድገት ላይ አስተዋጽኦ ለማድረግ ታትረን ተነስተናል፡፡
ሎሬት የኪነ-ጥበብ ማሰልጠኛ ተቋም እና ሚሊዮን ፊልም ፕሮዳክሽን ዕውቅና ካገኘበት ከ2010 ዓ.ም ጊዜ አንስቶ በኪነ-ጥበቡ ዘርፍ በስፋት እያስተማረ እና እየሰራ ይገኛል።






ግሎባላይዜሽን አለምን በተለያዩ የመረጃ ልውውጦች አንድ በማድረግ በተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚገኙ የህብረተሰብ ለቱኩስ መረጃዎች ቅርብ በማድረግ ረገድ በአንድ አገር ያለውን የኢኮኖሚ የቴክኖሎጂ እና የእድገት ልውውጦች በማስተሰሰር ላይ ይገኛል።
ኪነ-ጥበብን መዝናኛ ብቻ አርጎ ማሰብ ፍፁም ስህተት ነው። ለዚህም ይመስላል አለም ላይ ያሉ ታላላቅ ሃያላን ሀገራት ትልቅ መዋዕለ ንዋያቸዉን በማፍሰስ ትልቅ የጦር መሳሪያም አድርጎ በመጠቀም። ዜጎቻቸው ሀገር ወዳድ ሆነዉ እንዲያድጉ በመድረግ ለጦርነትም በወኔ በልበ ሙሉነት አነሳስቶ የማይታመኑ ጀብዶችን ያሳኩበታል። በምዕራቡ አለም ደሞ ባህላቸዉን በሌላዉ ላይ ለመጫን ጥቅም ላይ ሲያዉሉት ይስተዋላል። አሜሪካን ብንወስድ በእዉኑ ካደረገቻቸዉ ጦርነቶች ይልቅ በHollywood ያሸነፈቻቸዉ ጦርነቶቿ እልፍ ቁጥር የላቸዉም። በዚህም አለም ላይ የፈጠሩት ተጽእኖ ቀላል እንዳልሆነ እሙን ነዉ። ኪነ-ጥበብ የዚህች አለም ጣዕም እደመሆኑ መጠን ከእያንዳዱ ሰው እና ማህበረሰብ ክፍል ነጥሎ ማየትም ማሰብም ይከብዳል።
ኪነ-ጥበብ የአንድን ሀገር ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እሴቶቻችንን ትውፊት ባህሎቻችንን ለዛውን በጠበቀ ፣ አስተማሪና አዝናኝ በሆነ መልኩ ለማህበረሰቡ ለማቅረብ አንዱና ተመራጭ መንገድ ነው።
በተቋማችን ውስጥም በሞዴሊንግ ፣ በትወና ፣ በሁሉም ሙዚቃ መሳሪያ ስልጠና በመስጠት ፣ እንዲሁም በቪድዮ ኤዲቲንግ እያስተማርን ከ7,500 ሰው በላይ አስመርቀናል። በተለይ ለሴቶች እና ለህጻናት ፣ እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች 50% የክፍያ ቅናሽ አድርገን ስልጠና መስጠታችን ፣ በተጨማሪም፡- ለመንግስት ሰራተኞች በጉሩፕ ለሚመጡ ሰልጣኞች ሚኒቴሪዎችን ጨምሮ 50% ቅናሽ ማድረጋችን ልዩ ያደርገናል።
የስልጠና ቦታችን አነስተኛ ክፍል በመሆኑ ከአስተማሪዎች ጋር በቀጥታ አንድ ለአንድ ለመገናኘት ትልቅ ዕድል ይፈጥራል፡፡
ዋጋችን ኪስን በማይጎዳ ፣ የመዝናኛ ኢንዱስትሪውን በማያሳጣ በመሆኑ ለተማሪዎቻችን ተመራጭ ነው፡፡
ተማሪዎቻችን ከስልጠና በኋላ ሰፊ የስራ ዕድል በእኛ ተቋም በኩል እንዲያገኙ የራሳችንን ድርሻ እንወጣለን፡፡
አሰልጣኞቻችን በሙያው ጥልቅ ልምድ ያላቸው በመሆናቸው ለተማሪዎች ስኬታማነት ጉልህ የሆነ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡






